በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በስርአተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት ያደረገ ከተማ አቀፍ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር ተካሄደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በስርአተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት ያደረገ ከተማ አቀፍ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር ተካሄደ።

(ቀን ሚያዚያ 4/ 2016 ዓ.ም) በልምድ ልውውጡ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የልደታ ክፍለ ከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራና ክትትል አስተባባሪ አቶ ገዳ ሞሲሳ በጽህፈት ቤቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።            ...
በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃድ እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃድ እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

(ቀን ሚያዚያ 1/ 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ለመንግስት ትምህርት ተቋማት እውቅናና ፈቃድ ለመስጠት በተደረገ የምዘና ውጤት ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደዋል :: በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣ  ኃላፊዎችና በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሚገኙ...
ለህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።

ለህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።

(ቀን መጋቢት 18/2016 ዓ.ም)በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመክፈቻ ንግግራቸው  የአንድን ተቋም ሰላምና ደህንነት ፅዳትና ውበት መጠበቅ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ወሳኝ ነው በማለት ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ መሆኑን በመግለፅ ሰልጣኞች በትኩረት እንዲሳተፉ አደራ ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የህንፃ አስተዳደር...
የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ማርች 8 ን አከበሩ::

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ማርች 8 ን አከበሩ::

(ቀን መጋቢት 17/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ስርአተ ፆታ ክፍልና ሴት ኮከስ አባላት በጋራ በመሆን ማርች 8 የሴቶች ቀን አክብረዋል :: የሴቶችን የፆታ እኩልነትና መብት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ትግል እውቅና የምንሰጥበት ቀን ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ /ሮ በላይነሽ የሻው ቀኑን በማስመልከት...
ከከንቲባ ጽ/ቤት በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ተደረገ።

ከከንቲባ ጽ/ቤት በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ተደረገ።

(ቀን መጋቢት 16/2016 ዓ.ም) ለአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ  ከከንቲባ ጽ/ቤት በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል የተደረገ ሲሆን  በመድረኩ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። የድጋፍና ክትትሉ በዋናነት የፈተና ዝግጅት ያለበትን ሁኔታን ፣ እስከታችኛው  መዋቅር ያለውን የተማሪዎች የምገባ ስርአትን  እና ቅንጅታዊ አሰራር ያለበትን ደረጃ ያካተተ መሆኑ በድጋፍና...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

(ቀን መጋቢት 14/2016 ዓ.ም)  ድጋፉ በዋናነት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን እና ተቋማቱ ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተመረጡ 40ትምህርት ቤቶች የተደረገ ሲሆን ቢሮው ቁሳቁሶቹን ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች አስረክቧል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በርክክብ መርሀ ግብሩ...