ስለ ትምህርት ቢሮ

መነሻ ገጽ E የቢሮዉ አስተዳደር

ትምህርት የዕድገት ሁሉ መሰረት እንደመሆኑ መጠን መንግስት ትምህርትን ለልማት፤ለዲሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት በማመን ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አዲስ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ በመቅረፅ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የከተማውን ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ስር ነቀል ለውጦችን ለማምጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አቅዶ መፈፀምና ማስፈፀም የሚያስችል ስራዎችን በመስራት ላይ ነው፡፡ የህዝባችንን ኋላቀር አኗኗር ለመለወጥ ፍትህ’ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳዳርን በአስተማማኝ ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ትምህርት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማው ውስጥ የነበረውን የተወሳሰበ የትምህርት ሥርዓት ችግር ለመፍታት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ በርካታ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት’ መምህራንን በማሰልጠንና የትምህርት ግብአትን በማሟላት በትምህርት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት ባደረገው እንቅስቃሴ የትምህርት ሽፋንና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በተግባር ላይ በማዋል የከተማው ህብረተሰብ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ ፈጣንና ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን በማስመዝገብ ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በትምህርት ተቋማት ዉስጥ በልማት በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ግንባታ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የተሟላ ስብዕና ያላቸው ዜጎች ማፍራት!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የሥራ ኃላፊዎች

ዶክተር ዘላለም ሙላት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ወንድሙ ኡመር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ

አቶ አሊ ከማል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ

ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ

አቶ ሲሳይ እንዳለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

ወ/ሮ አበበች ነጋሽ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ

አቶ ጥላሁን ፍቃዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ

አቶ ዳኛቸው ከበደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቴክኒካል አማካሪ

የትምህርት አሃዛዊ መረጃዎች/ስታቲስቲክስ/

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም የተማሪዎች እና የተቋማት መረጃ (የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ)

የ2016 ዓ.ም ጠቅላላ የተማሪ ብዛት

የ2016 ዓ.ም የተቋማት ብዛት