የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

by | ዜና

(ቀን መጋቢት 14/2016 ዓ.ም)  ድጋፉ በዋናነት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን እና ተቋማቱ ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተመረጡ 40ትምህርት ቤቶች የተደረገ ሲሆን ቢሮው ቁሳቁሶቹን ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች አስረክቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በርክክብ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መሆኑን ጠቁመው የዛሬው ድጋፍ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት እንደተቀመጠው  በተቋማቱ ጫወታን መሰረት ያደረገ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ ክፍለ ከተሞችም ቁሳቁሶቹን በፍጥነት ወደትምህርት ቤቶች በማስራጨት ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በከንቲባ ጽህፈት ቤት የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ አማካሪ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን በበኩላቸው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ከጽንስ ጀምሮ እስከ ስድስት አመት ያሉ ህጻናትን መሰረት አድርጎ በከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸው ከፕሮግራሙ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ በመሆናቸው ክልሎችና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ልምድ እየወሰዱ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ተቀሟቱ የተደረገላቸውን የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ተጠቅመው ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነዘዴን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው ገለጻ አድርገዋል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ከተደረጉ ድጋፎች መካከል ምንጣፍ ፣ዥዋዥዌ፣ፍራሽ፣ሚዛን፣የህጻናትና መምህራን ጫማዎች ፣መሰላል፣አንሶላና ትራሶች እንዲሁም የጫማ መደርደሪያዎችን እና ተንቀሳቃሽ ሰሌዳዎች ይገኙበታል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 38
  • 257
  • 1,309
  • 8,085
  • 235,494
  • 235,494