ወቅታዊ ዜና

“ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነዉ፡፡

ቀን 16/9/2014 ዓ.ም "ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነዉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 የትምህርት ዘመን በከተማዉ የሚሰጠዉ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከምንጊዜውም...

read more

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የአፍጥር መርሀ-ግብር አከናወነ።

ቀን 20/8/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የአፍጥር መርሀ-ግብር አከናወነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት ባከናወነው  የአፍጥር መርሀ-ግብር  የቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪዎች ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ...

read more

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጠ፡፡

ቀን 6/8/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 12ኛ ክፍል ለሚያስፈትኑ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሀገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ ስርዓትን አስመልክቶ ኦረንቴሽን ሰጥቷል::የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በገለፃው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በምዝገባው ወቅት የሚፈጠሩ የመረጃ...

read more

በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በህዝብና በመንግስት የተገነቡ 82 ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ቀን 18/07/2014 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በህዝብና በመንግስት የተገነቡ 82 ፕሮጀክቶች ተመረቁ። በዛሬው እለት በልደታ ክ/ከተማ በህዝብና በመንግስት የጋራ ጥረት ሲገነቡ የቆዩ ከ162 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 82 ፕሮጀክቶች ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡ በፕሮጀክቶቹ ምርቃት ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት ለህዝብ...

read more

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ1ኛ ወሰነ ትምህርት በ12ኛ ክፍል ፈተና በፈተና ጥያቄዎች ውጤታማነት ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር አካሄደ።

ቀን 16/07/2014 ዓ.ም የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ1ኛ ወሰነ ትምህርት በ12ኛ ክፍል ፈተና በፈተና ጥያቄዎች ውጤታማነት ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር አካሄደ። በምክክር መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንደገለጹት የውጤት ትንተናው ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ለመስጠትና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያስችላል ብለው...

read more

”ትምህርት ቤቴን አጸዳለሁ፣ ጽዱና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል ሁሉን አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በይማነ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ቀን 09/07/2014 ዓ.ም ”ትምህርት ቤቴን አጸዳለሁ፣ ጽዱና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል ሁሉን አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በይማነ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ንቅናቄው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣የክፍለ ከተማና ወረዳ ኃላፊዎች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት በዛሬው እለት ተጀምሯል።...

read more

የምንሰጣቸዉ አገልግሎቶች

የትምህርት ማስረጃ

የአቻ ግመታ

የተቋማት ጥራት ኦዲት

የት/ት ቤት ስታንዳርድ

 

.

በተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊት የትምህርት ፍትሃዊነትን፤ተገቢነትንና ጥራትን በማረጋገጥ የብልፅግናችንን ጉዞ እናፋጥናለን!!

ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትምህርታዊ ዘርፍ ሽግግር

ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በትምህርት ዘርፍ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ቢሮዉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፕሮጄክቶችን በመቅረጽ በቢሮዉ አንዲሁም  በከተማዉ ዉስጥ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትቤቶች ዉስጥ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

School Net

ዲጂታል ትምህርት ቤቶች

በከተማዋ የሚገኙ ሁሉንም የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትቤቶችን በኔትዎርክ በማገናኘት የበይነ-መረብ የመስመር ላይ ት/ትና የተለያዩ ግብዓቶችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ዘመናዊ ኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ነዉ፡፡

የERP ሲስተም

በከተማዉ የትምህርት ቢሮ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችን የሥራ መረጃዎችንና የተለያዩ ግብዓቶችን መረጃ መዝግቦ ለመያዝና ለመቆጣጠር የሚያስችል አፕልኬሽን ነዉ፡፡

የፈተና ባንክ

ለተማሪዎች በአንድ ቦታ የተከማቹ የየክፍላቸዉን የተለያዩ የትምህርት ዓይነት የመልመጃ ፈተናዎችን የያዘ ሲስተም ሲሆን፤ትክክለኛዉ የጥያቄዉ መልስ የትኛዉ አንደሆነ እዛዉ ሲስተም ላይ ማወቅ የሚችሉበት ነዉ፡፡

AACEB የአንድሮይድ አፕ

ለተማሪዎችና ለመምህራን የሚያገለግሉ መፅሀፍትንና የኦንላይን ፈተናዎችን እንዲሁም የተለያዩ ጠቃሚ ግብዓቶችንና አገልግሎትችን የያዘ የአንድሮይድ ስልክ መተግበሪያ ነዉ፡፡