አገልግሎቶች

መነሻ ገጽ E አገልግሎቶች
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡-

ስለ እያንዳንዱ አገልግሎት ዝርዝር መረጃ ለማወቅ ከታች ይመልከቱ፡፡

የተቋማት ጥራት ኦዲት

ተቋማት የጥራት ኦዲት እንዲደረግላቸው የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ይጠበቁባቸዋል፡-

  • በተላከላቸው ቅጽ መሠረት የውስጥ ግምገማ ያደረጉበት ሪፖርት፣
  • ተቋሙ እውቅና/የዕድሳት የፈቃድ ማረጋገጫ
  • የተቋሙ ስም የትምህርት ደረጃ/መስክ

የትምህርት ቤት ስታንዳርድ

 

ድጋሚ ማስረጃ ቅድመ ሁኔታዎች

ድጋሚ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ አገልግሎት ለማግኝት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-

  • ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ ይዞ መቅረብ
  • ከፖሊስ የጠፋበት አፅፎ ማቅረብ አለበት
  • ከአንድ ዓመት ወዲህ የተነሱትን 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ
  • ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይገባዋል
  • ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 100.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል

 

የአቻ ግመታ ቅድመ ሁኔታዎች

የአቻ ግመታ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች :-

  • የትምህርት መረጃውን በተማሩበት አገር የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቦርድ ወይም District of education /council/ በጀርባው ላይ የባለስልጣኑ ስም፣ ቲተርና ማህተም እንዲሁም በተማሩበት ሀገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተምና ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት
  • የትምህርት መረጃው ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ውጪ የተጻፈ ከሆነ በኢትዮጵያ ህጋዊ መተርጎም ፈቃድ ባላቸው ድርጅቶች የተተረጎመና በተርጓሚው ድርጅት ማህተም የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል ፡፡
  • በትምህርት መረጃው የፈተና ውጤቶች በፊደል ወይም በቁጥር ከተሰጡ ምን ማለት እንደሆነ አቻ መገለጫ ያለው መሆን አለበት
  • የትምህርት መረጃና የሌሎች ማስረጃዎች ዋናና አንዳንድ ፎቶ ኮፒ መቅረብ አለበት
  • መረጃ ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይኖርበታል
  • ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 150.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል ፡፡

 

የስም ስህተት ለማስተካከል ሟሟላት ያለበት

 

  • ልደት ካርድ ኮፒና ዋናውን
  • ትራንስክሪብት ከ9 – 10 ወይም 11 – 12 ዋናውንና ኮፒ
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ
  • የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን
  • 1 ፎቶ ግራፍ እና 100.00 ብር