ለህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።

by | ዜና

(ቀን መጋቢት 18/2016 ዓ.ም)በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመክፈቻ ንግግራቸው  የአንድን ተቋም ሰላምና ደህንነት ፅዳትና ውበት መጠበቅ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ወሳኝ ነው በማለት ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ መሆኑን በመግለፅ ሰልጣኞች በትኩረት እንዲሳተፉ አደራ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዱኛ ድሪባ በበኩላቸው የተቋሙን ደህንነት እና ሰላም ፣ ፅዳትና ውበት ለመጠበቅ ለባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማሻሻያ ስልጠና በየጊዜው መስጠት ችግሮችን ለመፍታት ክፍተቶችን ለመሙላት ጉልበት እንደሚሆን የገለፁ ሲሆን ለሶስት ቀናት የሚቆየውን ስልጠና የሚወስዱት ነባርና አዲስ የጥበቃ ባለሙያዎችና የፅዳት ሰራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለሙዎች ናቸው  ብለዋል።

ስልጠናው  በጉለሌ ክፍለ ከተማ  የመነን አካባቢ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቅሩ ማሞ እና በፖሊስ ባልደረባዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው በሦስት ርዕሶት ላይ ማለትም የተቋም ደህንነትና ጥበቃ ፣ በእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ቅድመ መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም የተቋሙን ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ንብረቶችን እንዴት ማፅዳትና ተገቢ ጥንቃቄና ክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ በሚሉ ርዕሶች ላይ እንደሚያተኩር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 46
  • 257
  • 1,317
  • 8,093
  • 235,502
  • 235,502