የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ማርች 8 ን አከበሩ::

by | ዜና

(ቀን መጋቢት 17/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ስርአተ ፆታ ክፍልና ሴት ኮከስ አባላት በጋራ በመሆን ማርች 8 የሴቶች ቀን አክብረዋል ::

የሴቶችን የፆታ እኩልነትና መብት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ትግል እውቅና የምንሰጥበት ቀን ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ /ሮ በላይነሽ የሻው ቀኑን በማስመልከት ስንገናኝ ስለሴቶች ለመመካከርና ማድረግ ያለብንን ጉዳዮች ለመነጋገር መንገድ ይከፍትልናል ብለዋል ::

የአዲስ አበባ ሴት መምህራን ማህበር ሰብሳቢ ወይዘሮ እየሩሳሌም ብዙነህ በበኩላቸው የበአሉ አላማ የሴቶችን እኩልነት ማረጋገጥ እነደመሆኑ በሴትነቷ ሳትገፋ ማግኘት ያለባትን ሁሉ እንድታገኝ የምናበረታታበት ነው ያሉ ሲሆን  አያይዘውም የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የተገኙ ወንድ አጋሮችን አመስግነዋል ::

በአሉን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት ኮከስ ሊቀመንበር ወ /ሮ መስከረም አበራ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ማርች 8 ለምን እንደሚከበር እንዲሁም የሴቶች ዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ምን እንደሚመስል ያመላከቱ ሲሆን  በዘንድሮ በዓል አከባበር ላይም ሴቶችን በማሳተፍና በማብቃት ሰላምና ልማትን በማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበው ታዝማ የውስጥ ደዌና የሕፃናት ልብ ሕክምና ማእከል ለፕሮግራሙ መሳካት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል ::

ቀኑን በማስመልከት ከታዝማ የውስጥ ደዌና የሕፃናት ልብ ሕክምና ማእከል የተገኙት ዶክተር ሶፍያ ልኡልሰገድ እና የቀድሞ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንትና የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሴት ኮከስ አስተባባሪ የነበሩት ወ/ሮ መሰረት ካሳ የሕይወት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል ::

በአሉን አሰመልክቶም የተለያዩ ስነ-ፅሁፋዊ ሥራዎች ቀርበዋል ::

 

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 35
  • 257
  • 1,306
  • 8,082
  • 235,491
  • 235,491