የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም በ6ወራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ያከናወናቸውን ተግባራት ገመገመ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም)  በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት፣የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣የከንቲባና የፐብሊክ ሰርቪስ ጽህፈት ቤት የክትትልና ድጋፍ አመራሮች፣የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት ተወካዮች፣የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የወላጅ ኮሚቴ አመራሮችን ጨምሮ  ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የተሳተፉ ሲሆን የቢሮው የሪፎርምና የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ በ6ወራት በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ ከሚንቀሳቀስባቸው ተግባራት አንዱ የቅንጅታዊ አሰራር ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር በመፍጠር ባከናወናቸው የተለያዩ ተግባራት ውጤታማ ስራ መስራቱን በመግለጽ የትምህርት ስራ ለትውልድ ግንባታ ሂደት መሰረት የሚጣልበት ተግባር እንደመሆኑ ባለድርሻ አካላት ከቢሮው ጋር ቅንጅት ፈጥረው በመንቀሳቀስ ተቋሙ ያስቀመጠው ግብ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅንጅታዊ አሰራር መርህን ተግባራዊ በማድረግና ከተለያዩ ተቋማት ጋር  የስምምነት ፊርማ በመፈራረም በ2016 ዓ.ም በ6 ወራት ውስጥ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው የዛሬው መርሀ ግብር በ6ወራት ውስጥ በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ፣ የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ያሉበት ደረጃ ተገምግሞ በቀጣይ የትግበራ ጊዜያት የተሻለ ስራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው የ6 ወር ቅንጅታዊ አሰራር ሪፖርት ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ቅንጅታዊ አሰራር ለይስሙላ ሳይሆን ተጨባጭ ለውጥን ለማስመዝገብ በሚያስችል ደረጃ ከፍ ማለትና ወደተግባር  መቀየር  እንዳለበት ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል ቅንጅታዊ አሰራር ሚናው የጎላ እንደሆነና ትምህርት ቢሮ የጀመረው ተግባር ለሌሎች ተቋማትም አርአያ እንደሚሆን የሚሉት ከብዙህ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችየቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ምላሽና ማጠቃለያ የሰጡ ሲሆን በቅንጅት መስራት ለሀገር ግንባታ የሚጫወተው ሚና የጎላ በመሆኑ በቀሪ ስድስት ወራት ለተሻለ ስራ መተጋት ይገባል ብለዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 249
  • 119
  • 1,568
  • 7,362
  • 235,982
  • 235,982