ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም)  በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰኢድ አሊ፤የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል፣የቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እንዲሁም የክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እጅጋየሁ አድማሱ ተሳታፊ ሆነዋል።

                       

የመስክ ምልከታው ከተካሄደባቸው ተቋማት መካከል  ደጃዝማች ባልቻ አባነብሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ግንባታው በአጭር ጊዜ የተጠናቀቀውና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ የተለያዩ ቢሮዎች ፣ ካፍቴሪያ ፣ ላብራቶሪዎችን እና ቤተ መጽሀፍትን ጨምሮ የመምህራንን ስታፍ ያካተተ ባለ 4 ወለል ህንጻ የደረሰበት ደረጃ በአመራሮቹ የተጎበኘ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የቀሩ ጥቃቅን ስራዎች ባስቸኩዋይ ተጠናቀው ህንጻው የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አዝገንዝበዋል።

                               

ግንባታው በቅርቡ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ የሆነውና በፍሬህይወት ቁ.1 ትምህርት ቤት የሚገኘው ባለ 4ወለል የመማሪያ ህንጻም እንዲሁም መስከረም አንድ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው የተጀመረው ባለ 4 ወለል ህንፃ በአመራሮቹ የተጎበኘ ሲሆን መቅደላ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተከናወነ የሚገኘው የከተማ ግብርና ስራም ምልከታ ተካሂዷል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 312
  • 119
  • 1,631
  • 7,425
  • 236,045
  • 236,045