በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ።

በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ።

(ህዳር 21/2016 ዓ.ም) ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር  ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በውይይቱ በሰላማዊ የመማር ማስተማር አተገባበርን በተመለከተ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በአቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ...
የ2016 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመያ መርሀ- ግብር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ተጀመረ፡፡

የ2016 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመያ መርሀ- ግብር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ተጀመረ፡፡

(ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም)  በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ- ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት አመራሮች ፤ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር  ዶክተር እሸቱ ለማ  በመርሀ- ግብሩ መክፈቻ...
ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተጠናቀቀ።

ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተጠናቀቀ።

(ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም)  በዛሬው የማጠቃለያ ውድድር ቀደም ሲል ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳ ፣ ክፍለ ከተማና ከተማ ደረጃ በተካሄደ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከአማርኛ አምስት ከአፋን ኦሮሞ በድምሩ 10 የሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የተሳተፉ  ሲሆን ውድድሩም በዋናነት ህገ-መንግስትና የፌደራሊዝም ስርዓትን መሰረት አድርገው  በተዘጋጁ ጥያውቄዎች ላይ መሰረት በማድረግ ነው የተካሄደው ። የአዲስ አበባ...
በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘረጉ የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶችን በአዲስ መልክ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል የመስክ ምልከታ (sight survey) በመካሄድ ላይ ነው።

በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘረጉ የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶችን በአዲስ መልክ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል የመስክ ምልከታ (sight survey) በመካሄድ ላይ ነው።

(ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም)  የስኩል ኔት ፕሮጀክቱ ከ10 አመት በፊት ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት መማር እንዲችሉ ታስቦ በወቅቱ በነበሩ 74 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘረጋ ሲሆን መሰረተ ልማቱ ዳግም ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል  ኒው ዌቭ ሀይቲክ ሶሉሽን የተሰኘ ድርጅት ጨረታ በማሸነፍ ጥገናን ጨምሮ የጎደሉ እቃዎችን ለማሙዋላት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር መፈራረሙ ይታውቃል። የአዲስ አበባ...