የትምህርት ተቋማት የክፍል ፈተና አዘገጃጀትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ጥናት ግኝት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም)  ጥናቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለስልጣን ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ዳይሬክተሮች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማ ስርአተ ትምህርት አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለስልጣን የኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አንዋር ሙላት በከተማው በሚገ ኙ አንደኛ ፣ መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የክፍል ውስጥ ፈተና አፈጻጸም ሂደትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ጥናት ግኝት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ከፈተና አዘገጃጀት ጋር በተገናኘ ተግባራዊ መሆን ስለሚገባቸው መርሆች የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚያስችሉ አሰራሮች መካከል አንዱ የተማሪዎችን ዕውቀትና ክህሎት በአግባቡ መመዘን የሚያስችል የፈተና ስርአት መዘርጋት እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለስልጣን ያጠናውን ጥናት ግኝት መሰረት በማድረግ የተማሪዎችን ብቃት በትክክል የሚመዝን ፈተና ማዘጋጀት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 346
  • 119
  • 1,665
  • 7,459
  • 236,079
  • 236,079