የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ለመምህራን ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ለፍትሀዊነት ፕሮግራም በፌስ ሶስት ድጋፍ ከሚደረግላቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል የእንግሊዘኛና ሒሳብ መምህራን ነው የተሰጠው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን አሰልጣኝ ባለሙያና  የCCA ስልጠና አስተባባሪ ወይዘሪት ብርሀኔ በቀለ ስልጠናው ተከታታይ ምዘና አያያዝን መሰረት አድርጎ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል እንዲቻል 240 ለሚሆኑ መምህራን መሰጠቱን ገልጸው መምህራኑ የወሰዱት ስልጠና ምንያህል ውጤታማ እንደሆነ በየትምህርት ቤቱ በአሰልጣኞችና በስልጠናው አስተባባሪዎች ክትትል እንደሚደርግ አስታውቀዋል።

ባለሙያዋ አክለውም የዚህ ስልጠና ተሳታፊ መምህራን የሚያስተምሩባቸው ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ቀደም ብለው ተመሳሳይ ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመው ስልጠናው በየትምህርት ቤቱ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል ርዕሳነ መምህራኑ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

መምህር ዳንኤል ዘለቀ እና መምህር ሚኪያስ ምንዳ የእንግሊዘኛ እና ሒሳብ ትምህርት አሰልጣ  ኞች አስተባባሪ ሲሆኑ ስልጠናው ከ2012ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ በቆየባቸው አመታት በትምህርት ቤቶች ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ጠቁመው በቀጣይ እድሉን ያላገኙ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ስልጠና ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 213
  • 152
  • 1,464
  • 8,752
  • 235,195
  • 235,195