የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት ጾታን መሰረት አድርጎ የሚደርስ ጥቃትን ለመከላከል በወጣ አዲስ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው ከተመረጡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የስርአተ ጾታ ክበብ ተጠሪ መምህራን ጨምሮ ለክፍለከተማ የዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና ስርአተ ጾታ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ የወጣቶች ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ እስክንድር  በትምህርት ቤቶችና አከባቢ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መመሪያን መሰረት አድርገው ስልጠና ሰተዋል።

በትምህርት ቤቶችም ሆነ በአቅራቢያቸው በተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አሁንም ቢሆን አለመቆማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቁመው እነዚህን ጥቃቶች ለመከላከል በትምህርት ሚኒስቴር ተሻሽሎ የተዘጋጀው  አዲሱ መመሪያ ለትምህርት ማህበረሰቡ በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆንም ሆነ ጥቃቱን የመከላከል ተግባሩን ውጤታማ ለማድረግ የስልጠናው ተሳታፊዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም መመሪያው ለትምህርት ቤቶች በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆን ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ባለሙያ ወይዘሮ ትግስት በሪሁን በበኩላቸው በተማሪዎች ላይ  ለሚደርሱ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በተቋማቱ አከባቢ የሚገ ኙ አዋኪ ጉዳዮች ዋነ  ኛ ምክንያት መሆናቸውን ገልጸው መመሪያው እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በማሰብ በበርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከመዘጋጀቱ ባሻገር ጾታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በፍትህ ተቋማት የህግ ድጋፍ ያለው መሆኑን አስገንዝበዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም በቀረበው የስልጠና ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን በየትምህርት ቤቶቻቸው ጾታን መሰረት አድርጎ የሚስተዋሉ ጾታዊ ጥቃቶችን በማሳያነት በማንሳት ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 8
  • 175
  • 2,122
  • 9,143
  • 234,193
  • 234,193