የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  ዩኒፎርም በልካቸው እንዲቀርብ  ከወዲሁ እንዲለኩ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ተማሪዎቹን መለካት ያስፈለገው ከዚህ በፊት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ወጥ ሆኖ ተሰፍቶላቸው በሚቀርብ ወቅት ከተክለሰውነታቸው ጋር በተገናኘ እየጠበባቸው  መልበስ ሲቸገሩ ስለነበር  ችግሩን ለመቅረፍ  ታስቦ መደልኬት ስራ መገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎት/አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ልኬቱ በዋናነት ከየትምህርት ቤቱ በተሰበሰበ መረጃ መሰረት መለካት ያስፈልጋቸዋል ተብለው ለተለዩ 1112 ተማሪዎች ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በየክፍለከተማው በማዕከልነት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በቴክኒክና ሙያ ቢሮ ስር ካሉ ኮሌጆች በመጡ የልኬት ባለሙያዎች እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመው ተማሪዎቹን የመለካት ስራው ከተጠናቀቀ በኃላ ዩኒፎርም ለማቅረብ ጨረታ ላሸነፈ ድርጅት ዝርዝራቸው ተልኮ ልብሱ በስማቸው  ተሰፍቶ እንደሚቀርብላቸው አስረድተዋል፡፡

መምህርት አበባዬ ሽፈራው በኮከበ ጽበሀ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህር ሲሆኑ አንዳንድ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች  በሚጠቀሙት መድሃኒት ምክንያት ሰውነታቸው ስለሚጨምር ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በጋራ ተሰፍቶ የሚቀርብላቸውን ዩኒፎርም ለመልበስ ሲቸገሩ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን ተለክተው እንዲሰፋላቸው መደረጉ ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን እንደሚቀርፍ አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 3
  • 172
  • 1,613
  • 8,563
  • 234,833
  • 234,833