የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የመማር ብቃት ለመመዘን የተዘጋጀ ሰነድ መገምገም ተጀመረ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 26/2016 ዓ.ም)  የግምገማ መርሀ ግብሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው ሲሆን በግምገማው ከተመረጡ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን እና ከቢሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ በቀዳማዊ ልጅነት ፕሮግራም የህጻናትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመው ትምህርት ቢሮም ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 6 አመት የሆናቸው ህጻናት የትምህርት አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በርካታ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተቋማትን በመክፈት ለህጻናቱ ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነዘዴ ተግባራዊ ያደረገ ትምህርት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸው የህጻናቱን የመማር ብቃት ለመመዘን የተዘጋጀው ሰነድ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ምን ያህል ብቁ እንዳደረጉ ለመለካት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው ሰነዱ የህጻናቱን የመማር ብቃት ከመለካቱ ባሻገር የዕድገት ደረጃቸውን በአግባቡ መለካት የሚያስችሉ ሀሳቦችን ማካተቱን አስታውቀዋል።

የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ብቃትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ የመመዘኛ ሰነድ አቅርበው ገምጋሚዎቹ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ በጋራና በቡድን ሆነው ውይይት በማካሄድ ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ ከገምጋሚዎቹ የሚቀርቡ የማስተካከያ ሀሳቦች በሰነዱ ተካቶ የመማር ብቃት ምዘናው በየተቋማቱ እንደሚካሄድ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 273
  • 119
  • 1,592
  • 7,386
  • 236,006
  • 236,006