ዘንድሮ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የቅድመ አንደኛ ደረጃና አፋን ኦሮሞን እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ ለሚማሩ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ ገልጸው በሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሰጡ ሀሳቦችን በማካተት  የመማሪያ መጽሀፍቱን ለህትመት ዝግጁ በማድረግ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የግብረገብ ትምህርት(Barnoota safuu ) ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ በመተርጎምና የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ  በ2016ዓ.ም  ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች  ዝግጁ መደረጉን ጠቁመው ለትምህርት አይነቱ ግብአት ይሰጣሉ ተብለው የታሰቡ ተቋማት አስተያየት እንዲሰጡ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ  ዘንድሮ በአዲስ አበባ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ  ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ካደረጉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከመምህራንና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማስተካከያ ሀሳቦች መሰብሰባቸውን አቶ ሮቢ ጠቁመው እነዚህ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው መጽሀፍቱ  ለሁለተኛ ዙር ህትመት ዝግጁ መደረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 189
  • 217
  • 1,378
  • 8,772
  • 235,388
  • 235,388