በቅድመ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ትግበራ  የነበሩ መጽሀፍት ላይ የተሰጡ ግብዓቶችን በማካተተ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ለማድረስ ዝግጅት መጠናቀቁ ተመላከተ፡፡

ዘንድሮ ስርዓተ ትምህርቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የቅድመ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ገልጸው በሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሰጡ ሀሳቦችን በማካተት መጽሀፍቱን ለህትመት ዝግጁ በማድረግ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ጌታቸው አክለውም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የግብረገብ ትምህርት ወደ አማርኛ ቋንቋ በመተርጎምና የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በ2016 ዓ.ም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ዝግጁ መደረጉን ጠቁመው ለትምህርት አይነቱ ግብአት ይሰጣሉ ተብለው የታሰቡ ተቋማት አስተያየት እንዲሰጡ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

በተያያዘ ዘንድሮ በአዲስ አበባ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ካደረጉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከመምህራንና ከሌሎች ጉዳዩ በከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማስተካከያ ሀሳቦች መሰብሰባቸውን አቶ ጌታቸው ጠቁመው እነዚህ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው መጽሀፍቱ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  ለሁለተኛ ዙር ህትመት ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 21
  • 504
  • 2,657
  • 14,150
  • 227,934
  • 227,934