አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ለሚዘጋጀው የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሀፍ ይዘት ላይ ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) የማስተማሪያ መጽሀፉ በቢሮው የስርአተ ትምህርትና የገልማሶች ትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ትምህርቱን በሚያስተምሩ አመቻቾች  በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በመዘጋጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን አዘጋጆቹ በመረጡዋቸው ርዕሶች ይዘት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ ቢሮው የራሱን አቅም በመጠቀምና የአዲስ አበባን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የገልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ ውይይት በመጽሀፉ ይዘት ዙሪያ የሚሰጡ ሀሳቦች መጽሀፉን በአግባቡ በማዘጋጀት ወደ ህትመት ለመግባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

የቢሮው የልዩ ፍላጎት ጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት በበኩላቸው  የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን የሚማሩ አካላት ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ጋር ተዛማጅ የሆኑ ጽሁፎችን ማንበብ እንዲችሉም ሆነ በአከባቢያቸው ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተግባብተው  መኖር የሚያስችላቸውን ዕውቀትም ሆነ ክህሎት የሚያዳብሩበት መሆኑን ገልጸው በመጽሀፍ ዝግጅቱ እንዲካተቱ በተመረጡ ርዕሶች ዙሪያ በሚደረግ ውይይት የሚነሱ ሀ ሳቦች ተካተው ወደ ቀጣዩ ስራ የሚገባ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በውይይቱ የቢሮው የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ እና የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ማበልጸግ ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ በመጽሀፍ ዝግጅቱ መካተት በሚገባቸው የስርአተ ትምህርት ማዕቀፍና ይዘት ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን አቅርበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 1
  • 2
  • 119
  • 1,321
  • 7,115
  • 235,735
  • 235,735