የሰዓት አጠቃቀም ለውጤታማ ስራ ቁልፍ መሆኑ ተገለጸ፡፡

by | ዜና

(ቀን ጥር 27/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስራ ሰሃት መግቢያ በፊት ሰኞ ማለዳ በሚያዘጋጀው  የሰራተኞች የጋር  መአድ መቋደስ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተካፍለዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ እና ትግበራ ደይሬክቶሬት  ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ ጌታቸው ታለማ በሰዓት  አጠቃቀም  ጽንሰ ሀሳብና ተያየዥ  በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ሰራተኛው የሚያከናውናቸውን ስራዎች  የላቀ ለማድረግ አንዱ ጉዳይ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም መሆኑን በመጥቀስ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም ለመደበኛ ህይወትም የሚኖረው ሚና ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 119
  • 158
  • 1,412
  • 7,820
  • 235,733
  • 235,733