7ኛዉ ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በደማቅ ሁኔታ እንዲከናወን ላደረጉ አካላት የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቀረቡ፡፡

by | ዜና

ቀን 9/10/2014 ዓ.ም

7ኛዉ ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በደማቅ ሁኔታ እንዲከናወን ላደረጉ አካላት የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ምስጋና አቀረቡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዛሬ በወዳጅነት ፓርክ ‘’ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዛችንን በሳይንስ ፈጠራ ስራ እውን እናደርጋለን! ” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚያደርግ የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ደማቅ የመክፍቻ ስነ-ስርዓት አካሂዳል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ የኢፌዴሪ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ደምቀዉ ውለዋል፡፡

ተማሪዎች እና መምህራንም የፈጠራ ስራዎቻቸዉን ለማቅብ ችለዋል፡፡ የየክፍለ ከተማዉ ልዑካን ቡድኖችም ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በላቀ እና በደመቀ ደረጃ አሽብርቀዉ እና ተውበዉ እለቱን አድምቀዋል፡፡ ይህንንም አስመልክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የአውደ ርዕዩ የመክፈቻ መርሃ ግብር የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ በየደረጃዉ ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎች ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ለጸጥታ እና ለሚደያ አካላት ለነበራቸዉ የላቀ አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 83
  • 638
  • 2,110
  • 8,176
  • 236,940
  • 236,940