የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄደው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

ቀን 9/10/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀውና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄደው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከፈተ።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች፣መምህራን ፣ተማሪዎች እንዲሁም የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት በተማሪዎችና መምህራን የተዘጋጁት የፈጠራ ስራዎች ሀገራችን ለተያያዘችው የብልጽግና ጉዞ ዕውን መሆን የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸው በአውደ ርዕዩ የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች በከተማችን በትምህርት ዘርፉ እየታየ ያለው አበረታች ውጤት ቀጣይነትነት ላይ የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የፈጠራ ስራው እንዲስፋፋ በጀት ከመመደብ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ከለውጡ ቡኋላ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው ዘንድሮ በከተማ ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው አውደ ርዕይ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር ቀይረው የሚያሳዩበት ከመሆኑ ባሻገር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚፈጥርም አስረድተዋል።

የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በአውደ ርዕዩ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተግባር ተቀይረው ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ ገልጸው ተቋማቸው ሶስት ፈጠራዎችን መርጦ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው የፈጠራ ስራዎቹ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ወደ ላቀ ደረጃ መድረሷን የሚያሳዩ መሆናቸውን ጠቅሰው ተቋማቸው አምስት ፈጠራዎችን በመውሰድ ለአገልግሎት እንደሚያውል ገልጸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 274
  • 511
  • 2,649
  • 9,480
  • 234,005
  • 234,005