የአዲስ አበባ ከተማ አተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት መድረክ አካሄደ፡፡

by | ዜና

ቀን 19 /1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት መድረክ አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት የምስጋና በዓል መሆኑ ፤ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን የጨለማ ጊዜ አሳልፈኸን ብራን ልምላሜን ውበትን ያሳየኸን፤ ተፈጥሮን ሕይወትን መልሰህ ያጎናፀፍከን፤ መሬቱን በልምላሜ፣ ድፍርሱን በጥራት የተካህልን፤ ወደ ብርሃንና መልካም ዘመን ያሻገርከን ፈጣሪያችን ምስጋና ይገባሃል በማለት ምስጋናውን የሚያቀርብበት እና ላጠፋነው ነገር ሁሉ ይቅር በለን እያለ ከፈጣሪው ጋር ጥልቅ ተፈጥሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት በዓል እንደሆነ ተገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አድማሱ ደቻሳ በዓሉ የኦሮሞ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጫ እና በገዳ ሥርዓተ ትውፊት አማካኝነት ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ ድንቅ በዓል እንደሆነ የገለጹ ሲሆን በሁሉም ኢትዮጵያን የሚከበር በዓል ነው ብለዋል፡፡

የኢሬቻ የፓናል ውይይት መድረክ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጀምሮ በምርቃት እንዲጠናቀቅ የተደረገ ሲሆን የመወያያ ሰነዱ በቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ሲሳይ እንዳለ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ አቶ ሲሳይ በዓሉን ስናከብር በፍቅር፣ እርስ በእርስ በመተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሰላማችን የማረጋገጥ ሥራችንን እያጠናከን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 147
  • 152
  • 1,398
  • 8,686
  • 235,129
  • 235,129