ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የትምህርት አጀማመርን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ።

ቀን 11/1/2015 ዓ.ም

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የትምህርት አጀማመርን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ።

የመስክ ምልከታው በዋናነት ከፍተኛ ተማሪ ተቀብለው ወደ መማር ማስተማር ስራው በገቡ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብሬ ዳኘው፣ የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱን ጨምሮ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ናስር በምልከታው ተሳታፊ ሆነዋል።

ምልከታ የተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ተማሪ መቀበላቸውንና እስካሁን ምዝገባ ባለመቆሙ ተጨማሪ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ በመሆናቸው የተማሪ ክፍል ጥምርታው ከስታንዳርድ በላይ እንዲሆን ማድረጉን የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ ትምህርት ቤቶቻችን መቀበል ከሚችሉት በላይ ተማሪ ለመመዝገብ መገደዳቸውን ገልጸው በክፍለ ከተማው በቅርቡ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ ትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎቻቸውን  ፈረቃን ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅመው ማስተማር እንደሚገባቸው በመጥቀስ ቢሮው ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውዋል።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ናስር በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ያጋጠመውን የተማሪዎች የመማሪያ ክፍል እጥረት ለመቅረፍ የግለሰብ ህንጻ ተከራይቶ ከማስተማር ጀምሮ ተማሪዎችን በፈረቃ ማስተናገድ እና በግንባታ ላይ ያሉ ተጨማሪ ክፍሎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ ማድረግ የሚሉ አማራጮችን መሰረት በማድረግ ወደ አመቱ ትምህርት መገባቱን ጠቁመው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለችግሩ ትኩረት በመስጠት 5 ሚሊየን ብር መድቦ 536 የተማሪ መቀመጫ ዴስኮች ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረጉን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 161
  • 217
  • 1,350
  • 8,744
  • 235,360
  • 235,360