በክረምት በጎ ፈቃድ የትምህርት መርሀ-ግብር እየታገዙ መሆናቸውን ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

by | ዜና

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 2 ፣2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ስር በሚገኘው ሀምሌ 19/67 ትምህርት ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ ትምህርት መርሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በቀጣይ ዓመት የሚማሩትን  ትምህርት ቀድመው በመሸፈን ትምህርታቸውን ለማጠናከር እየረዳቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

መሀመድ አለዊ በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍለ ተማሪ እንደሆነና በዚህ በክረምት በጎ ፈቃድ ትምህርት መርሀ-ግብር ትምህርት ከጀመረ ሶስት ሳምንት እንደሞላውና በመጥቀስ በቀጣይ  ዓመት የሚማራቸውን ትምህርቶች ቀድሞ በመማሩ ትምህርቱን ለማጠናከር እንደረዳው ተናግሯል፡፡

የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ህይወት ተስፋዬ በበኩሏ የአጠቃላይ ሳይንስ፣ እንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርቶችን እየተማረች እንደሆነ የጠቀሰች ሲሆን ይህም በቀጣይ ዓመት ጥሩ ውጤታ ለማምጣት እንደሚያግዛት ተናግራለች፡፡

ሌላኛው የ7ኛ ክፍል ተማሪ  የሆነችው ትሁት ሰለሞን በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በመማሩዋ የእረፍት ጊዜዋን በአግባቡ በመጠቀም እንዳገዛት መናገራን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 1
  • 165
  • 2,159
  • 7,690
  • 241,700
  • 241,700