በትምህርት ተቋማት ሲካሄድ የቆየው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ውጤት አመላካቾች ምዘና ተጠናቀቀ።

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 2 ፣2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) ምዘናው  ሁሉንም የመንግሰት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በክፍለከተማ እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈትቤቶች እንዲሁም በትምህርት ቢሮ በሚገኙ አላማ ፈጻሚዎችና ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች የተካሄደ መሆኑን  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም በምዘናው ተሳታፊ ለሆኑ ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች ለመመዘኛነት በተዘጋጁ መስፈርቶችና በምዘናው ሂደት ላይ ቀደም ብሎ ኦረንቴሽን መሰጠቱን ጠቁመው ምዘናው በዋናነት የተቋማቱን የቁልፍ ውጤት አመላካች እቅድ ክንውንን መሰረት አድርጎ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮው ምዘና የተማሪዎች ውጤት በተለይም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጤት ከግምት ውስጥ መግባቱን አቶ ጌታሁን ጠቁመው በምዛው የተሻለ አፈጻጸም የሚያስመዘግቡ ተቋማት እውቅና እንደሚሰጣቸው አስገንዝበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 23
  • 898
  • 2,803
  • 8,663
  • 238,417
  • 238,417