(ቀን ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኤች አይቪ/ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለ4 ለአራዳ፣ ለአዲስ ከተማ ፣ ለቂርቆስና ለጉለሌ ክፍለ ከተሞች ለመጡ የመንግስት ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህራን እና ለጤና አጠባበቅ ክበብ ተጠሪ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰልጠና ሰጠ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ኢንዳሉት ማህበረሰቡ በኤች አይቪ/ ኤድስ ስርጭት ላይ ያለው አመለካከት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስቧል።
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት መንገሻ የተሰጠ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት ገንዘብ ደሳለኝ በወቅታዊ የኤች አይቪ/ ኤድስ ሰርጭት ፣ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የኤች አይቪ አጋላጭ እና ተጋላጭነት ሆኔታዎች አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ፣የኤች አይቪ /ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር የትኩረት አቅጣጫዎች እና ምን መደረግ አለበት በሚሉ ርዕሶች ላይ ስልጠናው ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።
0 Comments