በሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 19/2016 ዓ.ም)  ውድድሩ በገላን የወንዶችና በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚማሩ ተማሪዎች መካከል በየትምህርት አይነቱ የተካሄደ ሲሆን ለዛሬው ውድድር የቀረቡት ተማሪዎች ቀደም ብሎ በየትምህርት ቤታቸው በተካሄደ ተመ ሳሳይ ውድድር ተሳትፈው ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ተማሪዎች ናቸው።

በተማሪዎቹ መካከል የተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድሩ በአንደኛ ሴሚስቴር የተማሩትን ትምህርት መሰረት አድርጎ ከሁለቱ አቻ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ መምህራን በተዘጋጁ ጥያቄዎች እልህ አስጨራሽ ሆኖ መካሄዱን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የአዳሪና ሳይንስ ሼርድ ትምህርት ቤቶች ሱፐርቫይዘር አቶ ይልማ ተሾመ ገልጸው ውድድሩ በተማሪዎች መካከል የውድድር መንፈስ ከመፍጠሩ ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

አቶ ይልማ አክለውም አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ በውጤታቸው የተሻሉ የሆኑ ተማሪዎች እና የማስተማር ብቃታቸው የተረጋገጠ መምህራን ያሉባቸው እንደመሆኑ በ2016ዓ.ም  የዩኒ ቨርሲቲ መግቢያ ፈተና  የሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ በከፍተኛ ውጤት ማለፍ እንዲችሉ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ የዛሬው የጥያቄና መልስ ውድድርም የዚሁ ተግባር አንዱ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 46
  • 165
  • 2,204
  • 7,735
  • 241,745
  • 241,745