(ህዳር 11/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ የተቋማቱ የዝግጅት ምዕራፍ አጀማመር እና የተግባር ምዕራፍ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ በድጋፍና ክትትሉ የተሳተፉ አካላት ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ዘንድሮ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በሁሉም የትምህርት ተቋማት ድጋፍና ክትትሉ የሪፎርም ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ መካሄዱን ገልጸው ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት በየተቋማቱ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ እንደመካሄዱ በቀጣይ ግብረ መልሱን መሰረት በማድረግ ተቋማቱን ወደ ተቀራረበ የአፈጻጸም ደረጃ ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በዛሬው ውይይት በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች እና በወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ መቅረቡን የቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ጠቁመው በቀጣይ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የወረዳ እና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የክትትልና ድጋፉ ግብረ መልስ ቀርቦ ውይይት የሚካሄድ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ክትትልና ድጋፉ የትምህርት ተቋማቱ ከሪፎርም እና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ጋር በተገናኘ በዝግጅት ምዕራፍ የነበረውን አጀማመር እና በተግባር ምዕራፍ የነበሩ አፈጻጸሞችን መሰረት አድርጎ መካሄዱን የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኔ አስታውቀዋል።
በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
0 Comments