(ህዳር 17/2017 ዓ.ም) የጥያቄና መልስ ውድድሩ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት 8ኛ ክፍል በሚማሩ ተማሪዎች መካከል ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳ ፣ክፍለ ከተማና ከተማ ደረጃ ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው እለት በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣የትምህርት አመራሮች መምህራን እንዲሁም ተወዳዳሪ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው በተገኙበት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር እና ሀገራዊ እሴቶቻችንን በማበልጸግ እየተከበረ እንደሚገኝ ገልጸው በትምህርት ሴክተሩ በተማሪዎች መካከል ቀኑን አስመልክቶ የጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ ተማሪዎች ስለ ህገመንግስትም ሆነ ከፌደራል ስርአቱ ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል መርሀ ግብር መሆኑን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአል አስመልክቶ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ሲካሄድ ቆይቶ ለዛሬው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር መብቃቱን ጠቁመው ውድድሩ ተማሪዎች ስለ ህገመንግስት፣ፌደራል ስርአት እንዲሁም ከስነምግባር እና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው ሀገርን በማጽናት ሂደቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ የሚያግዝ መርሀ ግብር መሆኑን አመላክተዋል።
በዛሬው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍጻሜ ውድድር
በአማርኛው ስርአተ ትምህርት፡-
1ኛ.ተማሪ ሮቤራ ጠና 2ኛ. ተማሪ መዝሙር ሀዋዝ 3ኛ ተማሪ ናዳብ ተስፋዬ 4ኛ.ተማሪ ዮናታን ይታገሱ 5ኛ ተማሪ ያኔት ግርማ እንዲሁም
ከአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት
ተማሪ 1ኛ. ፌናን አየለ 2ኛ.ተማሪ ሀዊኔት ተማም 3ኛ. ተማሪ ሲንግተን ዘላለም 4ኛ.ተማሪ ጫላ ግርማ 5ኛ. ሲብራት በፍቃዱ በመሆን ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እና ከሌሎች የክብር እንግዶች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።
0 Comments