የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ከሚሰጡ የግል ትምህርት ቤት ባለሀብቶችና ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የነገ ተስፋ ህጻናት ለአዲስ አበባ በሚል መርሀግብር በቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘውተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕሮግራሙ አስተባባሪ በሆኑት በዶክተር ታቦር ገብረመድህን ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።

የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም የህጻናት ሁለንተናዊ እድገትን መሰረት አድርጎ የሚከናወን ፕሮግራም እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባለፉት አራት አመታት በመንግስት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመምህራን ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ገልጸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚሰጡ  የግል ትምህርት ቤቶችም ፕሮግራሙን በየትምህርት ቤቱ ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ የዛሬው ውይይት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበርክት አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ በበኩላቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ በከተማ አስተዳደሩ በቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚሰራው ስራ በግል ትምህርት ቤቶችም ተግባራዊ ሆኖ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችለው የትምህርት ተቋማቱ ባለሀብቶች ተገቢውን ግንዛቤ ይዘው ወደ ተግባር መግባት ሲችሉ እንደሆነ ጠቁመው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ፕሮግራሙ በየትምህርት ቤቱ ምን ያህል ተግባራዊ እንደተደረገ ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 6
  • 441
  • 2,188
  • 8,247
  • 237,387
  • 237,387