የዕውቀት ሽግግር ለራዕይ መሳካት ሚናው የጎላ መሆኑ ተመላከተ።

by | ዜና

(ቀን ጥር 20/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ባዘጋጀው  የሰራተኞች የጋር  የመአድ መቋደስ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎችና  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት በመገኘት ከቢሮ ሰራተኞች ጋር መዓድ ተካፍለዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ራዕይን ለማሳካት ከራዕይ መንደፍ ጽንሰ ሀሳብ እስከ ራዕይ መሳካት ሂደት ውስጥ መከናወን ሰለሚገባቸው መሰረታዊ  ጉዳዮች  ባቀረቡት ሰነድ ላይ አመላክተዋል፡፡

የእውቀት ስራ አመራር  ለተሻለ  ውጤታማ ስራ መሳካት የሚኖረዉን አበርክቶ አስመልክቶ  የሪፍርምና አገልግሎት አሰጣጥ  ክትትልና ድጋፍ  ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ ባቀረቡት የእውቀት ስራ አመራር  ሰነድ ላይ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  በመድረኩ የቀረቡ ሰነዶች የዕውቀት ሽግግርን በማጎልበት ለራዕይ መሳካት የሚኖራቸው ሚና ላቅ ያለ እንደሆነ በመግለጽ  ሰራተኛው የቀረቡትን ሰነዶች መሰረት በማድረግ ለስራ ውጤታማነት መትጋት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

             

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 2
  • 287
  • 119
  • 1,606
  • 7,400
  • 236,020
  • 236,020