የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

by | ዜና

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ነው፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ተለያዩ ከፍኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተመራቂዎች በየደረጃው የገጠሟችሁን ማህበራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ መሰናክሎችን ተሻግራችሁ እውቀት እና ጥበብን መርጣችሁ የትምህርት ዓላማችሁን በስኬት አጠናቃችሁ ለዚህ ክብር ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ኢትዮጵያን በማገልገል ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎች ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል፥ 2 ሺህ 420 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 2 ሺህ 438 ያህሉ ደግሞ በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

ከድህረ ምረቃ ተመራቂዎች መካከል 131 ያህሉ በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 239 ያህሉ ደግሞ በስፔሻሊቲ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 1 ሺህ 654 ሴቶች ናቸው፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 162
  • 152
  • 1,413
  • 8,701
  • 235,144
  • 235,144