የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

by | ዜና

ቀን 27/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የመሩት ሲሆን በውይይቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የትራፊክ ጽህፈት ቤት አመራረችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎችና የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑና የፈተናው ሂደትም በበላይነት በትምህርት ሚኒስቴር የሚመራ ቢሆንም ከተማ አስተዳደሩ ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ዘላለም አክለውም ቀደም ሲል ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቃማት አመራሮች ጋር መሰል ውይይቶች መካሄዳቸውን ገልጸው ቢሮው ከነገ ጀምሮ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ጣቢያ የሚያጋጉዙ ተሸከርካሪዎችን ማዘጋጀቱን በመግለጽ የጸጥታ አካላት ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲካሄድ የተለመደ ተግባራቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 117
  • 152
  • 1,368
  • 8,656
  • 235,099
  • 235,099