የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት መረጃ  አስተዳደር  ቡድን የ2015 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት መረጃ ያለበትን ሁኔታ የክፍለ ከተማ የቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪዎች በተገኙበት ገመገመ።

የ2015 ዓ.ም መረጃን ለመሰብሰብ በትምህርት ሚኒስተር የበለጸገውን ስታት ኢዱ(stat edu) ሶፍትዌር  በመጠቀም  መረጃዎች እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በአግባቡ እንዲሰበሰቡ ቀደም ሲል ለክፍለከተሞች ኦረንቴሽን መሰጠቱን እና በአሁኑ ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎችን የማጥራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ ገልጸው ጥራቱን የጠበቀና ተአማኒነት ያለው መረጃ መሰብሰብ ለአጠቃላይ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መሰረት በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብርሀም በበኩላቸው የትምህርት መረጃን በአግባቡ መሰብሰብ ትምህርት ቤቶች ባላቸው የተማሪ ብዛት የሚላክላቸው የድጎማ በጀት በአግባቡ እንዲመደብ ከማስቻሉ ባሻገር መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ለሚከናወኑ የተለያዩ ትምህርታዊ ተግባራት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በ2015ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከ የትምህርት መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ መሰረት በክፍለ ከተሞች አማካይነት መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደ ዳታ ቤዝ ኢንኮድ የማድረግ ተግባር መከናወኑን በመግለጽ  የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማጥራት ለትምህርት ሚኒስቴር እንደሚላክም አስታውቀዋል።

በመርሀግብሩ የቢሮው የሶፍትዌርና ዳታ ማዕከል ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን በቡድኑ በቀጣይ ከማዕከል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ አዲሱን አደረጃጀት መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 25
  • 898
  • 2,805
  • 8,665
  • 238,419
  • 238,419