የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሠራተኞች ስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።

by | ዜና

(ቀን ጥር 25/2016 ዓ.ም)  “አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሰራተኞች ስልጠና መድረክ ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛ ቀን የስልጠና መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት  ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ  ጥላሁን ፍቃድ  በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግስት ሰራተኞች ሚና በሚል ርዕስ የስልጠና  ሰነድ  ካቀረቡ በሀላ ሰራተኞች ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በማጠቃለያ መድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ሀገራችን እየሄደችበት ያለውን ሂደት ውጤታማ  ለማድረግ  እየተደረገ ላለው እንቅስቃሴ ፐብሊክ ሰርቫንቱ  የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ ታሳቢ ተደርጎ ስልጠናው መሰጠቱን ጠቁመው  በሰላም ጉዳይ ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸው ያለ ሰላም ወጥቶ መግባትና መንቀሳቀስ የማይታሰብ መሆኑን በመገንዘብ ለሰላም መስፈን ከመንግስት ጎን በመቆም መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀላፊው አክለዉም ብቃት ያለው ፐብሊክ ሰርቫንት በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና ተሰናስሎ በመስራት  ገዢ ትርክቶቸን በማስቀጠል ከልዩነትና ብሔርተኝነት አስተሳሰቦች ይልቅ በልማትና በጎ አስተሳሰብ ላይ በጋራ በመሆን ለላቀ ስራ መትጋት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 2
  • 87
  • 2,308
  • 8,342
  • 238,527
  • 238,527