የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሠራተኞች ስልጠና መድረክ የከሰሃት ውሎ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።

by | ዜና

(ቀን ጥር 24/2016 ዓ.ም)  “አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሰራተኞች ስልጠና መድረክ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ በአቶ አሊ ከማል ሀብት መፍጠር እና ማስተዳደር እንዲሁም በገዢ ትርክት ግንባታ ዙሪያ ሁለት ሰነዶች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ በአቶ ሲሳይ እንዳለ ተጨማሪ  ሰነድ ቀርቦ በቢሮው ሠራተኞች  ሰፊ ውይይት ተካሂደውባቸዋል።

በስልጠናው የከሰሀት ውሎ በሰራተኞች ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በሰጡት ማጠቃለያ  ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር የአገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን መገንባት እና ሀብቶቻችንን በአግባቡ ማስተዳደር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ውይይቱም በሌሎች ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በነገው እለት የሚቀጥል መሆኑን ከመድረኩ ተገልጿል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 87
  • 44
  • 2,792
  • 8,479
  • 238,525
  • 238,525