የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አፈጻጸም ዙሪያ ሂደቱን ለመከታተል ከተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

by | ዜና

ቀን 22/10/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አፈጻጸም ዙሪያ ሂደቱን ለመከታተል ከተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

በውይይቱ የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተማ የሰላምና የጸጥታ እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ፈተናው ዘንድሮ ከሰኔ 27 እስከ 29/2014 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የፈተና አፈጻጸም ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፈተና ህትመት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የፈተና ሂደቱ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የትምህርት መዋቅሩ እንደተለመደው ከፖሊስም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የጸጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በ2014 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71,832 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱና ለሁሉም ተማሪዎች አድሚሽን ካርድ መታደሉን ጠቅሰው በፈተናው ወቅት ከጣቢያ ኃላፊ ውጭ ማንኛውም አካል ሞባይል ይዞ ወደፈተና ጣቢያ መሄድ እንደማይችል በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ዘንድሮ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች 1,800 ፈታኝ ፤ 450 ሱፐር ቫይዘር ፤ 179 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ በድምሩ 2,429 የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸው የተገለጸ ሲሆን ከቢሮ ጀምሮ እስከ ፈተና ጣቢያዎች ድረስ የፈተናውን ሂደት የሚከታተል ኮማንድ ፖስት እንደተዋቀረም ተገልጻል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 119
  • 158
  • 1,412
  • 7,820
  • 235,733
  • 235,733