(ህዳር 9/2017 ዓ.ም) “ህዳር ሲፀዳ” በሚል መሪ ቃል በተቋማት የተጠራውን ከተማ-ዓቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ማልደው የስራ ከባቢያቸውን አፅድተዋል።
የሁለቱም ተቋማት አመራርና ሰራተኞች በተሳተፉበት በዚህ የፅዳት ዘመቻ የመስሪያ ቤቱ ቅጥር ጊቢን ጨምሮ በተቋሙ ዙሪያ የሚገኙ ስፍራዎች ፀድተዋል።
በፅዳት ረገድ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመዲናችንን ገፅታ ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ እየተቀየረ መምጣቱ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ፅዳት ቀጣይነት ኖሮት አከባቢያችንን ማፅዳት ባህላችን አርገን መውሰድ መቀጠል የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተግልጻል።
“ውስጣችንን ከጥላቻ አካባቢያችንን ከቆሻሻ እናፅዳ!”
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ዲዛይንና ግንባታ ቢሮዎች አመራሮችና ሰራተኞች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡
0 Comments