የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት እና የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬቶች የዘርፉን የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ።

by | ዜና

(ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም) ዳይሬክቶሬቶቹ የ6 ወራቱን ተግባራት ለማሳካት እቅድን ከማውረድ ጀምሮ ተግባራትን ተቀናጅቶ ለማስፈፀም የተሰራው ሥራ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በመርሀ ግብሩ ላይ በስድስቱ ወራት በሁለቱም ዳይሬክቶሬቶች የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው በዚህ ሂደት የተከናወኑ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማስቀጠልና በአፈጻጸም  የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ውጤታማ ስራ ለመስራት ዳይሬክቶሬቶቹ ሰፊ ተግባር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል ።


በመርሃ ግብሩ የቢሮ ፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ ስርዓተ ትምህርትና ትምህርት በሬዲዮ  አተገባበርን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭት ጣቢያ ኃላፊ አቶ አብይ ተፈራ እንዲሁም ፣ የስርአተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ አቶ ጌታሁን ጌታቸው  6 ወራት የተሰሩ ሥራዎችን አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን የክፍለ ከተማና ወረዳ ናሙና የ 6ወር ሪፖርቶችም ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል ::

በውይይቱ የዳይሬክቶሬቶቹን ባለሙያዎች ጨምሮ የክፍለ ከተማና ወረዳ አማርኛ የስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎችና ባለሙያ  ተሳታፊ ሆነዋል።

0 Comments