የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና


(ህዳር 9/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ፕሮግራም ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ረቢራ ዱጋሳ በመልካም አስተዳደር ጽንሰ ሀሳብ ላይ ያጠነጠነ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የመልካም አስተዳደር ችግሮቸን መፍታትና የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና ማቀላጠፍ ወሳን መሆኑን ጠቅሰው ሰራተኛዉ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

0 Comments