ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት ለተከታታይ ሶስት አመታት ሲጠየቅ የቆየውን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የጃራ አባገዳ ትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪዎች መማርያ ፤ የአስተዳደር ህንፃ ፤ የላይብረሪና የላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች የግንባታ ስራ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

by | ዜና

ቀን 29/9/2014 ዓ.ም

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት ለተከታታይ ሶስት አመታት ሲጠየቅ የቆየውን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የጃራ አባገዳ ትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪዎች መማርያ ፤ የአስተዳደር ህንፃ ፤ የላይብረሪና የላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች የግንባታ ስራ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የህዝብ ጥያቄ ከነበረባቸው አንዱ የሆነው ይህ ትምህርት ቤት ግንባታው ከዚህ ቀደም የነበረውን የቅበላ አቅም ከ405 ወደ 1500 በማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ ወቅት እንደተናገሩት የህዝብን አንገብጋቢ ችግር ቅድሚያ ሰጥተን እንፍታ ብለን በመፍታት ሂደት ላይ ነው ያለነው፤ ትምህርት ቤቱም የዛ ማእቀፍ አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር አለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኘ እና ህገ-መንግስታዊም መብት ነው ያሉ ሲሆን ፤ በሌሎች የሃገራችን ክልሎች በበርካታ የሃገራችን ቋንቋዎች ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም ተማሪዎች በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በተለያየ አለም አቀፍ ቋንቋዎችም በግሪክ፣ በፈረንሳይኛ በአረብኛ ፣ በቱርክና በመሳሰሉት ይማራሉ፤ የአገራቸውንም ባንዲራ ይሰቅላሉ፣ የሀገራቸውንም መዝሙር ይዘምራሉ ፣ ከራሳቸው ቋንቋ አንዱ በሆነው በኦሮምኛም መማር ከጀመሩ ዋል አደር ብልዋል ያሉ ሲሆን ነገር ግን አንዳንዶች ይህንን ስህተት እንደተሰራ አስበው የፖለቲካ አጀንዳ ያደርጉታል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አብዛኛዎቹ የኦሮምኛ ቋንቋ ትምህረት የሚሰጥባቸው አካባቢዎች ከተማዋ ስታድግና ስትስፋፋ የሄደችባቸው አካባቢዎች ፤የነበረ ነባር ቋንቋ: ባህልና የማንነት መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን ልጆች እየተሸማቀቁ ማደግ የለባቸውም፤ በነፃነት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር አለባቸው በማለትም ገልፀዋል፡፡ ይሄንን የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ካልሆነም ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አስተዳደሩ የሚገደድ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ላይ የኦሮምኛ ቋንቋ የትምህርት ካሪኩለም ስለሌለ የኦሮምያን ስርዓተ ትምህርት ይጠቀም እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ሰአት የኦሮምኛ ቋንቋን የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት ተሰርቶ ተጠናቋል ብለዋል፡፡አዲስ አበባ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን ለአለም አቀፍ ተቋማት መልካም ቤት ሆናለች ፤ያሉት ከንቲባ አዳነች የራስዋን ልጆች የምታሸማቅቅ እንድትሆን ለማድረግ የሚጥሩ አካላት መሰረታዊ ስህተት እየፈፀሙ ስለሆነ በፍጥነት መታረም አለባቸው፡፡ ስለሆነም ህዝባችን ግን የሃሰት ፖለቲካ ነጋዴዎች የሚያቀርቡላችሁን የተለያየ ብዥታ መፍጠርያ አጀንዳ ቆም ብላችሁ እንድታስተውሉት እጠይቃለሁ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 32
  • 152
  • 2,295
  • 8,185
  • 241,405
  • 241,405