አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በእንግሊዘኛ ቋንቋ  የተዘጋጀው የግብረገብ (Barnoota safuu )ትምህርት ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ በመተርጎም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የትርጉም ስራው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላለው የትምህርት እርከን የተዘጋጀውን የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍ፤የመምህር መምሪያ እንዲሁም መርሀ ትምህርቱን የሚያካትት መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዜግነት ትምህርት ባለሙያው አቶ መለሰ ዘለቀ ገልጸው በትርጉም ስራው ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው የእንግሊዘኛ እና ሲቪክስ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ አቶ መለሰ አክለውም የግብረገብ ትምህርት መጽሀፍ የመተርጎም  ስራው ሲጠናቀቅ በየደረጃው ከመምህራን እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት የሚስተካከሉ ሀሳቦች ተካተው ወደህትመት እንደሚገባ ጠቁመው በአዲስ አበባ በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች የግብረገብ ትምህርት(Barnoota safuu ) እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 61
  • 441
  • 2,243
  • 8,302
  • 237,442
  • 237,442