አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራኖች ስልጠና ተሰጠ ::

by | ዜና

(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ  ጋር በመተባበር አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራኖች  የ2ኛ ቋንቋ የመማር ማስተማር ስነ ዘዴና ስትራቴጂ ፣ የ2ኛ ቋንቋን የመማር ማስተማር ክህሎት እና የ2ኛ ቋንቋን በልምምድ ማስተማር የሚያስችላቸው ስነ ዘዴዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ጀምራል ::

ቀደም ሲል ቢሮው ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ሁለተኛ ቋንቋዎችን በተመለከተ ጥናትና ምርምር ውጤት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን  በጥናትና ምርምሩ ግኝት መሰረት ስልጠናው መሰጠቱ አማርኛና አፋንኦሮሞ ቋንቋዎችን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራን የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሚሆን ተገልፃል ::

በስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል እና የመምህራንና የት/ት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ አድማሱ የስልጠናውን ሂደት በአካል በመገኘት ምልከታ አድርገዋል ።

የቢሮው ኃላፊ  ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ሰልጣኞች በሁለት ቀን ቆይታቸው ከአሰልጣኞች የሚያገኟቸውን እውቀቶች እና ክህሎቶች እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ የብዝሀ ቋንቋ ሀገራዊ ሀብታችንን ለማጎልበት እንደ ሁለተኛ ቋንቋ በሚሰጡ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ትምህርቶች ላይ ትርጉም ያለው የቋንቋ እድገት ለውጥ ለማምጣት የበለጠ መትጋት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል::

ስልጠናው በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ ሲሆን አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን እንደ 2ኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መምህራን እየተሳተፉ ይገኛሉ ::

0 Comments