በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ውጤት የተሻለ መሆኑ ተመላከተ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 ተማሪዎች መካከል፡- 

1.  50 ከመቶ እና በላይ  ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 3.3 በመቶ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 19.8 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸው፤

2.   በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 እና በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 273 ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 125 ተማሪዎች በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው፤

3.  እንደ ሀገር እጅግ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ትምህርት ቤቶች መካከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  10 ትምህርት ቤቶች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው፤ በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ተፈታኝ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ውጤት አንጻር በጣም አስደሳችና አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ይሁን እንጂ ውጤቱ ገና የሚቀረው በመሆኑ በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የሚናችሁን እንድትወጡ አደራ እያልን ለተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ! ለማለት እንወዳለን፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 152
  • 1,251
  • 8,539
  • 234,982
  • 234,982