በሁሉም የመንግሰት ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱ እየተመራ የሚገኝበትን ሰርዓት የተመለከተ ግምገማዊ ሱፐርቪዥን ተካሄደ፡፡

ሱፐርቪዥኑ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለተካታታይ ሶስት ቀናት የተካሄደ ሲሆን ሱፐርቪዥኑም በዋናነት በየትምህርት ቤቱ ያለው አመራር አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራውን በምን አግባብ እየመራው እንደሚገኝ ለማወቅ ታስቦ የተካሄደ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዝን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዬ አሰፋ ሱፐርቪዥኑ 39 ነጥቦችን በያዘ ቼክ ሊስት መሰረት  ሱፐርቪዥኑን ለሚያካሂዱ  ለ2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች እና የቢሮ ሱፐርቫይዘሮች ኦረንቴሽን ተሰቶ መካሄዱን ገልጸው የሱፕርቪዥኑ አላማ ትምህርት ቤቶች ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን በማከናወን የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ እንዲያሟሉ፣ የተማሪዎች ውጤት እና ስነ-ምግባር በሚፈለገው ደረጃ እንዲሻሻል ለማድረግ አመራሩ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ማስቻል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ ወይዘሪት ትግስት ድንቁ በበኩላቸው ሱፐርቪዥኑ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት በመገምገም ትምህርት ቤቶች ተቀራራቢና ውጤታማ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ታስቦ መካሄዱን ጠቁመው በየደረጃው ያለ የትምህርት አመራር የአመራርነት ሚናውን እንዴት እየተወጣ እንዳለ በመገምገምና የሚታዩ የአፈፃፀም ችግሮችን በመፈተሽ ክፍተቱን ለማረም ሱፐርቪዥኑ እንደሚረዳም አስረድተዋል፡፡ የሱፐርቪዥኑ ተሳታፊዎችም በየትምህርት ቤቱ በነበራቸው ቆይታ አብዛኞቹ ርእሳነ መምህራን በፍቃደኝነት የሚጠየቁትን መረጃ በማቅረብ ተባባሪ እንደነበሩ ጠቅሰው በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ግን ከመረጃ አያያዝ ጀምሮ አንዳንድ ችግሮች መስተዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 257
  • 217
  • 1,446
  • 8,840
  • 235,456
  • 235,456