(ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ እቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የሪፎርምና አገልግሎት ክትትል ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬቶች በጋራ በመሆን በአገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ምንነት እንዲሁም ስትራቴጂክ እቅድን እስከታች ካስኬድ ማድረግና ሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ስሌት አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ቀደም ሲል በ11ዱ ክፍለ ከተሞች ክትትልና ድጋፍ መደረጉን አንስተው በድጋፍና ክትትሉ ውጤት መሰረት ፍረጃ በመስጠት የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ልምዳቸውን በመቀመር ለሌሎቹ እንዲያሳልፉ መደረጉን ተናግረው በድጋፍና ክትትሉ የታዩ እጥረቶችን ለመሙላት ቢሮው ስልጠናውን ማዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡
በሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች የተዘጋጀው ስልጠና በድጋፍና ክትትል ስራ ከአገልግሎት አሰጣጥና መደበኛ ስራዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የታዩ እጥረቶችን ለመሙላት ያስችላል ያሉት አማካሪዋ ሰልጣኞች በስልጠናው ከሚነሱ ርእሰ ጉዳዮች በመነሳት ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበርና አገልግሎት አሰጣጥና ሪፎርም ስራዎች የሚያጋጥሙ እጥረቶችን በመሙላት በሁሉም የትምህርት ተቋማት ተቀራራቢ ውጤት እንዲኖር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
እቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ስልጠናው በ1ኛ እና 2ኛ ሩብ አመት በተደረገ ድጋፍና ክትትል የታዩ ክፍተቶች መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸው እቅድን በአግባቡ ለማቀድና ተግባር ላይ ለማዋል ሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ሂደት አሰራርን ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባና ባለሙያዎችና ቡድኖች በእቅድ ዝግጅት ወቅት የሚቀረጹ አላማዎችን በአግባቡ በመረዳት ስትራቴጂን የማውረድ አቅም ውስንነት ለማሻሻል እንዲሁም ስትራቴጂውን ከበጀት ጋር ማያያዝና ተግባራትን በስታንዳርዱ መሰረት ለመፈጸም አቅም የሚፈጥርላቸው ስልጠና እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ቢሮው በልምድ ልውውጦችና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች በማዘጋጀት የታዩ ጉድለቶች እንዲሞሉና የተቋማትን የመፈጸምና ማስፈጸም አቅም ከፍ ለማድረግ የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡
ስልጠናው የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥና ስታንዳርዳይዜሽን አስተባባሪ በሆኑት ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር በአገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ምንነት ላይ ፤ በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ በሆኑት አቶ እንዳልካቸው አማካኝነት እቅድን እስከታች ካስኬድ ማድረግ ፤ ሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ስሌት አሰራር ላይ ትኩረት በማድረግ ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች፤ የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments