የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

                                     

በመርሀ ግብሩ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የስርዓተ ትምህርትና ቴክኖሎጂ አስተባባሪ አቶ ስለሺ ሶሪ በስነ ምግባር ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የቀረበው ሰነድ ስራችንን በምናከናውንበት ወቅት ልንከተላቸው የሚገቡ የስነ ምግባር መርህዎችን ተረድተን አገልግሎት አሰጣጣችንን በውጤታማነት ለማከናወን ያግዛል ብለዋል፡፡

                                 

0 Comments