(ቀን 5/4/2017 ዓ.ም) ውይይቱ በዋናነት በሬዲዮ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ በትምህርት ቤቶች የተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስን እና የሬዲዮ ትምህርቱ ከስርአተ ትምህርቱ ጋር ምን ያህል ተቀናጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ከ1ኛ ደረጃ ምክትል ርዕሳነ መምህራን እና ከክፍለ ከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች ጋር ነው የተካሄደው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የውብዳር አያሌው ቢሮው የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ የሬዲዮ ትምህርት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በዛሬው መርሀግብር የሬዲዮ ትምህርት ተግባራዊ በሚደረግባቸው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አተገባበሩ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ የተደረገ ድጋፍና ክትትል ግብረ ላይ በመወያየት በቀጣይ የሬዲዮ ትምህርቱን በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንደሚያግዝ አመላክተዋል።
የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ቡድን መሪ አቶ አብይ ተፈራ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረገው የሬዲዮ ትምህርት ከስርአተ ትምህርቱ ጋር ምንያህል ተቀናጅቶ እየተተገበረ እንደሚገኝ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ተ ሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አንስተው በስራ ክፍሉ ምላሽ ተሰቷል።
0 Comments