(ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም) በውይይቱ በድጋፍና ክትትሉ የተሳተፉ የክፍለከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ያካሄዱትን ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጸጋዬ ሁንዴ ድጋፍና ክትትሉ በከተማ አስተዳደሩ ከ2011ዓ.ም ጀምሮ በተቋቋሙ 90 የድጋፍ መስጫ ማዕከላት መካሄዱን ጠቁመው በድጋፍና ክትትሉ በቀረበው ግብረመልስ መሰረት በቀጣይ የተሻለ ስራ በመስራት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከድጋፍ መስጫ ማእከላቱ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በቅንጅት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ የልዩ ፍላጎት ጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በበኩላቸው የአካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በማሰብ በከፍተኛ በጀት እንደመቋቋማቸው ቢሮው በማዕከላቱ የሚገኙ የድጋፍ መስጫ ግብአቶች ለተማሪዎች በአግባቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን በድጋፍና ክትትል የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡
ዳይርክተሩ አያይዘውም ከጎልማሶች ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ የተሸለ ስራ ሰርተው ሞዴል የሆኑ የማስተማሪያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ጠቁመው የነዚህን ጣቢያዎች ተሞክሮ ወደሌሎች በመውሰድ ትምህርቱ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
0 Comments