(ቀን 1/04/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የስርዓተ ፆታ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ለ 33ኛ በሀገራችን ለ19 ኛ ጊዜ የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ ፆታ ጥቃት ቀን የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት አክብሯል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው ባደረጉት ንግግር በአሉን ስናከብር ሴቶች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው የምንማማርበትና ራሳችንም ጥቃት ላለመፈፀም ቃል የምንገባበት እንዲሁም በሀገራችን ከቀን ወደቀን ባህሪውን እየቀየረና ተስፋፍቶ እየተፈፀመ ያለውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም የራሱን ኃላፊነት በመወጣት ጥቃት እንዲቆም የምንከላከልበት ሊሆን ይገባል ብለዋል ::
አያይዘውም የትምህርት ተቋማት በነዚህ 16 የፀረፆታ ጥቃት ቀናት ለተማሪዎች በፆታዊ ጥቃት ላይ ግንዛቤ የምንሰጥበትና ራሳቸውን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ግንዛቤ የምንፈጥርበት መሆን አለበት ብለዋል ::
በበአሉ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጤና ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ መኮንን ፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀንን መነሻ ያደረገ የውይይት ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ::
ዕለቱን አስመልክቶ ከብሄራዊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጡ ተማሪዎች መዝሙር ቀርቧል ::
0 Comments